Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ወግ ብሄራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ በሚል ርዕስ የውይይትና የምክክር መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ወግ ብሄራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ በሚል ርዕስ የውይይትና የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ የሚገኘው የብሔራዊ የማህበረሰብ ተኮር የምክከር መድረክ አንዱ አካል የሆነው የታሪክ ምሁራንና የታሪክ ፀሐፊያን የምክክር መድረክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ለአራት ቀናት በቢሾፍቱ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል፡፡

የዚሁ አካል የሆነው ‘የሰላም ወግ ብሄራዊ መግባባት ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ በሚል ርዕስ የውይይትና የምክክር መድረክም ዛሬ ተካሂዷል።

ባለብዙ ደርዝ የሆነውን የሃገሪቱን ችግር በእውቀትና በትክክለኛ ይዞታቸው ቃኝቶ መፍትሄ ማበጀት የበለጸገችውን ሃገር ለማየት እንደሚያስችል የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል ገልጸዋል።

ተደራራቢ የሃገሪቱ ችግሮች ውስጥ የሚጠቀሰው ታሪካዊ ይዘትም ፍጹም ነጻና በእውቀት ላይ ተመስርቶ ውይይት በማካሄድ ለብሄራዊ መግባባትና ለዘላቂ ሰላምና ሃገር ግንባታ ያግዛል ብለዋል።

መድረኩ በተለያዩ የታሪክ እና ሌሎች የትምህርት መስክ ምሁራን የታሪክ የፖለቲካና የማህበራዊ ሳይንስ ጥናትና ምርምር ለብሄራዊ መግባባትና ለሃገር ግንባታ ያለውን አበርክቶ የዳሰሰ ነበር፡፡

በመድረኩ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ተሳታፊዎች ውይይት አድርገውበታል።

በተስፋዬ ከበደ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.