Fana: At a Speed of Life!

ኮማንድ ፖስቱ ተልዕኮውን በቁርጠኝነት በመወጣቱ አንፃራዊ ሰላም ማምጣት ችሏል- ጄኔራል አበባው ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር የክልሉ ሕዝብ እና ኮማንድ ፖስቱ በወሰደው የተቀናጀ እርምጃ አንፃራዊ ሰላምን ማምጣት መቻሉን የጦር ኀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ገልጸዋል።

ጄኔራል አበባው ታደሰ ከሰሜን ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ መሪዎች፣ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ከጎንደር ከተማ አሥተዳደር እና ከወረዳ ኮማንድ ፖስት መሪዎች ጋር በአሁናዊ የጸጥታ ሁኔታና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የቀጣናው አሁናዊ የሰላም ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ መሻሻልን አሳይቷል ያሉት ጄኔራል አበባው÷ ጽንፈኛው ኀይል በተወሰደበት እርምጃ አቅሙን በማጣቱ ምክንያት የሽፍታነት ባህሪን ለመላበስ ተገዷል ብለዋል፡፡

የባሕርዳር-ጎንደር ኮማንድ ፖስት በቡድኑ ላይ በወሰደው እርምጃ እና በፈፀመው አኩሪ ገድል የቡድኑ የኔትወርክ ትስስር ተበጣጥሷል ነው ያሉት፡፡

እርስ በራሱ ወደ መበላላት ደረጃ በመውረድ፣ ተስፋ በመቁረጥ ሕዝቡን የመዝረፍ፣ የማሰቃየት፣ የውንብድና እና የዘራፊነት ተግባር በመፈፀም ላይ እንደሚገኝም መግለጻቻን የመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች ኀላፊነታቸውን በቁርጠኝነት ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.