Fana: At a Speed of Life!

የቆላማ አከባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አተገባበር  ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቆላማ አከባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አተገባበር ዙሪያ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማንና  የክልሉ ካቢኔ በተገኙበት በጅግጅጋ ተገመገመ።

በቆላማ አከባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አተገባበር እና ባሉት ተግዳሮቶች ላይ በሰላም ሚኒስቴር የተደረገ ጥናትና አጠቃላይ ሂደቱን በተመለከተ ውይይት እና ግምገማ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ተካሂዷል።

በውይይት መድረኩ ላይ የሰላም ሚኒስቴር በቆላማ አከባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ዙሪያ እስካሁን የተሰሩ ስራዎች ዙሪያና አጠቃላይ ሂደቱን ጥናት በማቅረብ ውይይትና ግምገማ ተደርጎበታል።

በውይይቱም ላይም የሶማሌ ክልል አርብቶ አደሩ ሰፊ ድርሻ እንደመያዙና ባለው የድርቅ ስጋትም ለፕሮጀክቱ የተያዘው የፋይናንስ ሁኔታ በቂ እንዳልሆነ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ተነስቷል።

በመድረኩ ላይ የተሳተፉ የሰላም ሚኒስቴር ተወካዮች በሰጡት ምላሽም የፉይናንስ ስርዓቱ የሚከወነው በሀገሪቱ ሁኔታ መሠረት እንደሆነ የገለፁ ሲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ድርቅን መቋቋም የሚችል ማህበረሰብ ለመፍጠር እየሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር  አቶ ሙስጠፋ ሙሀመድ የቀረበው ማብራሪያ አጥጋቢ እንደሆነ ገልፀው ከመድረኩ የተነሱ ሀሳቦችን እንደግብአት በመውሰድ ፕሮጀክቱን ውጤታማ እንዲሆን መሳሰባቸውን ኤስአርቲቪ ዘግቧል።

ፕሮጀክቱ ለስድስት አመት በተመረጡ ስድስት የሀገሪቱ ክልሎች የሚተገበር ሲሆን በሶማሌ ክልል 36 ወረዳዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.