Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ማሳደግ በዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው-አቶ መላኩ አለበል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ በዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ፡፡

በሞጆ ከተማ የሚገኙ የቆዳ ኢንዱስትሪዎችን የጎበኙት አቶ መላኩ አለበል በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ የግል ሴክተሮችን በቅርበት መደገፍ እና ማበረታት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በከተማዋ ከሚገኙ 27 ያህል መካከለኛ እና ከፍተኛ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ 19 የሚሆኑት የተሻለ ምርት እያመረቱ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በበጀት ዓመቱ በከተማዋ ከሚገኙ የቆዳ ኢንዱስትሪዎች 90 ሚሊየን ዶላር ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢንዱስትሪዎቹ ባለፉት አምስት ወራት የእቅዳቸውን 73 በመቶ ማሳካት መቻላቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ በዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ÷ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.