Fana: At a Speed of Life!

ለ200 ሆቴሎች ዳግም የደረጃ ምደባ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዚህ ዓመት ለ200 ሆቴሎች ዳግም የደረጃ ምደባ ለማካሄድ እቅድ መያዙን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በዚህ ዓመት በሀገሪቱ የሚገኙ ሁሉንም ሆቴሎች ዳግም በደረጃ ለመመደብ ከአዲስ አበባ ሆቴል ባለሃብቶች ጋር ውይይት አድርጓል።

በዚህም በ2008 ዓ.ም በኮከብ ደረጃ የተመደቡ ሆቴሎች የደረጃ ምደባ ደንብና መመሪያ በሚያዘው መሠረት በየሶስት ዓመቱ በድጋሚ መመደብ ያለባቸው በመሆኑ በ2012 ዓ.ም ለ200 ሆቴሎች ዳግም ደረጃ ምደባ ለማካሄድ እቅድ ተይዟል ነው ያለው።

በአገልግሎት ጥራት ተወዳዳሪነትነና የሆቴል ደረጃ ምደባ ስርዓት የነበሩ ሂደቶች ቀርበው ውይይት እንደተካሄደባቸውም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.