Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

 በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ቸርነት ጉግሳ ሁለቱንም የባህርዳር ከተማ ግቦች በፍጹም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር÷ የወልቂጤን ብቸኛ ግብ ደግሞ ፉዓድ አብደላ አስቆጥሯል፡፡ በውጤቱ መሰረትም የጣና ሞገዶቹ ነጥባቸውን 37 በማድረስ  ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ያሉ ሲሆን ÷ወልቂጤ ከተማ በ16 ነጥቦች ወራጅ ቀጠና ላይ ይገኛል፡፡ የክለቦቹ 19ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ የባህርዳር…
Read More...

በማንዴላ ዋንጫ የአፍሪካ ቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ 6 ሜዳሊያ በመሰብሰብ አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዴላ አፍሪካ ቦክስ ውድድር ኢትዮጵያ ሶስት ብርና ሶስት የነሐስ በአጠቃላይ ስድስት ሜዳልያ በማግኘት ውድድሩን አጠናቃለች። በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያ በሱራፌል አላዩ፣ ሚሊዮን ጨፎ እና ቤተል ወልዱ የነሃስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ ቤተልሄም ገዛህኝ፣ ሮማን አሰፋ እና ተመስገን ምትኩ ደግሞ…

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ማንቼስተር ሲቲ ለዋንጫ ይፋለማሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ እና ማንቼስተር ሲቲ የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫን ለማንሳት ይፋለማሉ፡፡ ማንቼስተር ዩናይትድና ኮቬንትሪ ሲቲ ዛሬ ያደረጉት ጨዋታ መደበኛና በጭማሪ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3 አቻ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡ በዚህም ዩናይትድ በመለያ ምት 4 ለ 2 በማሸነፍ ለዋንጫው መፋለም የሚያስችለውን ድል…

ሊቨርፑል ፉልሃምን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ፉልሃምን የገጠመው ሊቨርፑል 3ለ 1 አሸንፏል፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው አጋማሽ አንድ አቻ ሆነው ወደ መልበሻ ክፍል ቢያመሩም ከዕረፍት መልስ ሊቨርፑል ባስቆጠራቸው 2 ጎሎች ፉልሃም ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎም በ74 ነጥብ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር እኩል…

ኤቨርተን፣ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄዱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ኤቨርተን፣ ክሪስታል ፓላስ እና አስቶንቪላ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ በዚህም ኤቨርተን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ክሪስታል ፓላስ ዌስትሃምን 5 ለ 2 ረትቷል፡፡ እንዲሁም ከመመራት ተነስቶ አስቶንቪላ ቦርንማውዝን 3 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የተገናኙት ኢትዮጵያ ቡና እና መቻል አንድ አቻ ተለያይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቡናን ጎል አማኑኤል አድማሱ በጨዋታ ሲያስቆጥር የመቻልን ጎል ደግሞ ምንይሉ ወንድሙ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡

በ41 ዓመቱ ፈጣኑን የማራቶን ሠዓት ያስመዘገበው አትሌት – ቀነኒሳ በቀለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን በተካሄደው የማራቶን ውድድር ከ40 ዓመት በላይ በሆናቸው አትሌቶች ከ2019 ወዲህ ፈጣኑን ሠዓት በማስመዝገቡ አድናቆት ተችሮታል፡፡ አትሌት ቀነኒሳ የዛሬውን የለንደን ማራቶን ውድድር 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል፡፡ የዓለም አትሌቲክስም አትሌቱ…