Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ሁለት የውጭ ሀገር ተጨዋቾችን አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ሁለት የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን ለሁለት ዓመት ኮንትራት ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡ ክለቡ ናይጀሪያዊው ሞሰስ ኦዶ ቶቹኩን እና ጋናዊውን አማካይ ክዋሜ አዶምን ማስፈረሙን የክለቡ መረጃ ያመላክታል፡፡ ኦዶ ቶቹኩ በሀገሩ ናይጄሪያ፣ ግብፅ፣ ኢራን፣ ሳይፕረስ፣ ሱዳን እና ቻይና ሊግ ረዘም ያለ የእግር ኳስ ሕይወት ማሳለፉ ተገልጿል፡፡ ጋናዊው የ26 ዓመት የተከላካይ አማካይ አዶም ፍሪምፓንግን በስዊድኑ ዳልኩርግ ክለብ እንዲሁም በሀገሩ ክለቦች አሻንቲኮቶኮ እና…
Read More...

በሴቶች የዓለም ዋንጫ ብራዚል እና ጣሊያን ከውድድሩ ተሰናበቱ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኒውዝላንድ እና አውስትራሊያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የሴቶች የዓለም ዋንጫ ወደ ጥሎ ማለፍ የተቀላቀሉ ቡድኖች ተለይተዋል። በውድድሩ ብራዚል እና ጣሊያን ሳይጠበቅ ከምድባቸው ተሰናብተዋል። በምድብ 6 ከፈረንሳይ፣ ጃማይካ እና ፓናማ ጋር የተደለደለችው ብራዚል ከምድቡ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ከጥሎ ማለፉ ውጭ…

ኢትዮጵያ በሴካፋ ከ18 ዓመት የሴቶች እግር ኳስ ውድድር በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበራት(ሴካፋ) ከ18 ዓመት በታች የሴቶች የእግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዛንዚባር አቻውን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። በቻማዚ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የአጥቂ መስመር ተሰላፊዋ እሙሽ ዳንኤል በ45ኛ፣ በ55ኛ እና በ56ኛ ደቂቃ…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታ አሜሪካ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለወዳጅነት ጨዋታ አሜሪካ ገብቷል፡፡ ዋልያዎቹ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ያረፉ ሲሆን÷ በሚቀጥሉት ቀናት ልምምድ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ ቆይታው ሐምሌ 26 በዋሽንግተን ዲሲ ከጋያና ብሔራዊ ቡድን እናሐምሌ 29 በሳውዘርን ክረሰንት ስታዲየም ከአትላንታ ሮቨርስ…

ቢኒያም በላይ እና ዮሴፍ ታረቀኝ የውድድር አመቱ ኮከቦች በመሆን ተመረጡ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተጫዋች ቢኒያም በላይ የ2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመረጠ። ‘የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፎትቦለርስ አሶሴሽን’ እንዳስታወቀው ተጫዋቹ፥ በየክለብ አምበሎች በተደረገ ምርጫ ቀዳሚ በመሆን የውድድር አመቱ ኮከብ ሆኖ ተመርጧል። ቢኒያም በላይ በዚህ የውድድር አመት ክለቡ…

ማንቼስተር ዩናይትድ ከአዲዳስ ኩባንያ ጋር ትልቁን የመለያ ውል ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ማንቼስተር ዩናይትድ ከጀርመኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ አዲዳስ ጋር ለቀጣይ 10 ዓመታት ተጨማሪ ውል መፈራረሙን አስታወቀ። በውሉ መሰረትም ማንቼስተር ዩናይትድ ከጀርመኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ጋር ያላው የውል ሥምምነት እስከ ፈረንጆቹ ሰኔ 2035 ድረስ ይቆያል ነው የተባለው፡፡ በዚህም…

ቅዱስ ጊዮርጊስና ባሕር ዳር ከተማ ነገ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ቅዱስ ጊዮርጊስና ባሕር ዳር ከተማ ነገ ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ። ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም ጋር የተደለደሉት ፈረሰኞቹ ÷ ነገ ቢሾፍቱ በሚገኘው ክብር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ዝግጅታቸውን በይፋ እንደሚጀምሩ ታውቋል። ፈረሰኞቹ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ነሐሴ 12 ወይም 13/2015 ዓ.ም…