Fana: At a Speed of Life!

በቦሌ ክ/ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ ወደ ሱቅ የተላከ የ10 ዓመት ህፃን ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቦሌ ክፍለ ከተማ በመኖሪያ ቤት እና በንግድ ሱቅ ላይ በደረሰ የመኪና አደጋ የ10 ዓመት ህፃን ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ።
አደጋው የደረሰው በሲኖትራክ ተሽከርካሪ ሲሆን፥ ተሽከርካሪው የመንገድ ጠርዝ ስቶ አንድ ላይ ተያይዘው የሚገኙ የመኖሪያ ቤት እና የንግድ ሱቅ ጥሶ በመግባት ባደረሰው አደጋ ወደ ሱቁ ተልኮ የመጣ አንድ የ10 ዓመት ህፃን ልጅ ህይወት ማለፉን የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መርማሪ ምክትል ሳጅን ታምራት መስፍን ተናግረዋል፡፡
በአደጋው በሁለት ግለሰቦች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም ከፍተኛ የንብረት ውድመት መድረሱንም ነው የተናገሩት፡፡
የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ሌሎች ህፃናትን ይዘው ባይሸሹ ጉዳቱ እጅግ የከፋ ሊሆን ይችል ነበር ተብሏል፡፡
በሰው ህይወትና በንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነስ አሽከርካሪዎች በሀላፊነት ስሜት ሊያሽከረክሩ እንደሚገባም ምክትል ሳጅን ታምራት መስፍን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.