Fana: At a Speed of Life!

ትግራይ ሥርዓት አልበኝነት የሰፈነባት የስቃይ ማዕከል ሆናለች – ትዴፓ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትግራይ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ልጆች ወደ ጦርነት የሚጋዙባትና ሥርዓት አልበኝነት የሰፈነባት የስቃይ ማዕከል ሆናለች ሲሉ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቱ (ትዴፓ) የፖለቲካ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ አለማየሁ ተናገሩ።

አቶ ተስፋዬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ትግራይ ትምህርት ቤቶችና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እስር ቤት የሆኑባት የአፍሪካ ጓንታናሞ ሆናለች ብለዋል።

የኢትዮጵያን መንግስት ይደግፋሉ ተብለው የሚታሰቡ የሚታሰሩበት፣ ለአቅመ አዳምና ሄዋን ያልደረሱ ህፃናት ወደ ጦርነት የሚሰማሩባት የስቃይ ማዕከል መሆኗንም ተናግረዋል።

“የአፍሪካው ጓንታናሞ ቤይ የትግራዩ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲ፣ የአገልግሎት ተቋማት፣ ሆቴሎች እነዚህ በሙሉ እስር ቤት ሆነዋል።
ሁለት ይዞታ አላቸው፤ እነዚህ አንደኛው የኢትዮጵያን መንግስት ይደግፋል፣ የአብይን መንግስት ይደግፋል ብለው የሚያስቡትን የሚያስሩበት ነው።

ሁለተኛው ለአቅመአዳምና ሄዋን ያልደረሱ ልጆች ወደሌላ አካባቢ ሾልከው እንዳይወጡ የሚያደርጉበትና ወደ ጦርነት በሄዱ ቁጥር አንዱ ዲቪዥን፣ አንዱ ብርጌድ፣ አንዱ የመቶ፣ አንዱ የሻምበል፣ አንዱ የሻለቃ፣ ባለቀ ቁጥር ይሄኛውን አውጥተህ የምታስገባበት ነው።” ብለዋል።

ቡደኑ ለብቻው የሚፈነጭባት፣ የሕዝብ እስር ቤትና የባርነት ቀንበር የተጫነባት ትግራይን መመስረት እንጂ በስልጣን ላይ እያለ ያልደገፈውን ሕዝብ የመደገፍ ዓላማ እንደሌለውም አስረድተዋል።

የቡድኑ አባላት የትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ እንደማይደራደር ስለተረዱ ከተቀረው ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹ ሊያጣላው ሲጥር እንደነበረም ነው አቶ ተስፋዬ የተናገሩት።

የቡድኑ አባላት ኢትዮጵያዊ የሆነ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የአስተዳደር ፍልስፍና ያልነበራቸው የውጭ ሀይሎች ተልዕኮ አስፈፃሚ የነበሩ ናቸው ብለዋል።

አሸባሪወ ቡድን በስልጣን ላይ በነበረ ጊዜ “ግብጾች ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ይፈልጋሉ” ሲል ክስ ሲያቀርብ ቢቆይም አሁን ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራ መሆኑን በግብጽ ሚዲያ መግለጹ በምን ያህል ቅዥት ውስጥ እንዳለ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

አሸባሪው ህወሓት የትግራይን ሕዝብ ከሌሎች ኢትጵያዊ ወንድሞቹ ጋር የመነጠል ድብቅ አጀንዳ ይዞ ሲንቀሳቀስ እንደነበር የገለፁት አቶ ተስፋዬ፤ ቡድኑ በግብጽ ሚዲያ ያነሳው ሃሳብም ይህንኑ እኩይ ዓላማውን ያንፀባረቀበት እንደሆነም ጠቁመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.