Fana: At a Speed of Life!

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢሂ አብዲ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢሂ አብዲ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ።
 
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በጉብኝቱ ላይ ተሳትፈዋል።
 
በፕሬዚዳንቱ የተመራው ልዑክ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ተዟዙሮ ጎብኝቷል።
 
የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ የፓርኩን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ያስጎበኙ ሲሆን÷ፓርኩ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት እያደረገ ያለው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያም ሰጥተዋል።
 
ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ በጉብኝቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው÷ በተመለከቱት የስራ እንቅስቃሴ እንደተደነቁ መናገራቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴቢህ አብዲ የተመራ ልዑክ ሀዋሳ ከተማ መግባቱ የሚታወስ ነው።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.