Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ያለልዩነት ኢትዮጵያን ያስከበሩበት ድል ነው- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአድዋ ድል በባርነት ስር ለነበሩ ጥቁር ህዝቦች ሁሉ የነጻነት የሞራል ስንቅ መሆኑ ተገለጸ።

የአድዋ ድል ባርነትን ከማሸነፍ በላይ መሆኑን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ በዓል አከባበር ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት የአድዋ

ድል የኩሩ ህዝቦች ተጋድሎ አርማ ነው ብለዋል።

የአድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ያለልዩነት ኢትዮጵያን ያስከበሩበት እና ሁሉም ነገር ከሀገር በታች መሆኑን ያሳዩበት ነው ብለዋል።

አሁንም አንዳችን ለሌላችን ድጋፍ መሆን ይገባናል ብለዋል በመልዕክታቸው።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አድዋ የአሸናፊነትና የአይበገሬነት ምልክት ነው ብለዋል።

የዛሬው ትውልድ ከጥንት ወገኖቻችን ጽናትና ጥንካሬን በመውረስ ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር ጥላቻን በማሸነፍ የጋራ ሀገራችንን መገንባት ይኖርብናል ነው ያሉት።

በታሪክ ከምንጣላ የዛሬውን ድህነት በማሸነፍ የትውልዱን ታሪክ በደማቅ ቀለም መጻፍ ይኖርብናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ጥንታዊ አባት አርበኞች ፕሬዚዳንት ልጅ ዳኒኤል ጆቴ ወገኖቻችን በጽናት ታግለው አሸናፊነትን አውርሰውናል ብለዋል።

የአሁኑ ትውልድም ልዩነትን በመተው የጋራ ሀገር መገንባት ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

የህዳሴውን ግድብ ግንባታ መጨረስ ላይ ትኩረት አድርገን እንስራ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው በበኩላቸው ጥንት ቤተሰቦቻችን በሺህ ኪሎሜትሮችን በመጓዝ ለመላው ጥቁር ህዝቦች ወኔ የሆነ አሸናፊነትን አስመዝግበዋል ብለዋል።

የአድዋ ድል የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን በባርነት ስር ለነበሩት ሁሉ የሞራል ስንቅ ነበርም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.