Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የተመራው የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን ጋር ተወያየ።
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ከ45 በላይ አባላት እንዳሉት ተገልጿል፡፡
በተመረጡ የምርጫ ጣቢያዎች በመዘዋወር ቅድመ ምርጫ ፣ የምርጫ ቀን እና በድህረ ምርጫ ያሉትን እውነታዎች እንደሚታዘብ ቡድኑ አብራርቷል።
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ከመሆኑም በላይ የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦባሳንጆን በቡድን መሪነት መመደቡን አመስግነው ለቡድኑ መልካም የሥራ ጊዜ መመኘታቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.