Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ትራምፕ እየተቀጣጠለ የመጣውን አመጽ ለማረጋጋት ጦር ሰራዊት እንደሚያዘምቱ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 25 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፖሊስ የተገደለውን የ46 ዓመቱን ጥቁር አሜሪካዊ የጆርጅ ፍሎይድን ሞት ተከትሎ እየተቀጣጠለ የመጣውን አመጽ ለማስቆም የጦር ሰራዊት እንደሚያሰማሩ አስታወቁ።

በሚኔሶታ ሚኒያ ፖሊስ የ46 ዓመቱ ጆርጅ ፍሎይድ በግፍ መገደል ምክንያት በማድረግ የተቀሰቀሰው የተቃውሞ ሰልፍ ወደ አመጽ ከመቀየሩም ባለፈ ወደ ሌሎች የአሜሪካ ከተሞችና ግዛቶች ተስፋፍቶ ሰባተኛ ቀኑን ይዟል።

በርካታ ከተሞች የሰዓት እላፊ ገደብ ቢያወጡም ሰልፎች የወጡትን ገደቦችና መመሪያዎች ችላ በማለት በተቃውሞ አመጻቸው መቀጠላቸው ተገልጿል።

በዚህም ፕሬዚዳንቱ የአሜሪካ ከተሞችና የግዛት አስተዳዳሪዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን ተቃውሞ መፍትሄ መስጠት ካልቻሉ በደንብ የታጠቁ ወታደሮችን ልኬ እኔ አስቆመዋላሁ ሲሉ ዝተዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዋይት ሀውስ ውስጥ ሆነው መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ፖሊሶች የአስለቃሽ ጭስና እና አድማ መበተኛ የፕላስቲክ ጥይት ሲተኩሱ ይሰማ ነበርም ተብሏል።

ጆርጅ ፍሎይድን ጉሮሮውን በጉልበቱ ረግጦ በመግደል ተጠርጥሮ የተከሰሰው ዴሪክ ቾቪን በሦስተኛ ደረጃ ነፍስ በማጥፋት ወንጀል ተከሶ ወህኒ ቤት የሚገኝ ሲሆን÷ በሚቀጥለው ሳምንት ፍርድ ቤት ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

ከፖሊስ መኮንኑ ጋር በወቅቱ አብረው የነበሩት ሦስት የፖሊስ መኮንኖች ከሥራ የተባረሩ ሲሆን፥ እስከዛሬም ድረስ በቁጥጥር ሥር አለመዋላቸው ብዙ ሰልፈኞችን አስቆጥቷል።

ምንጭ፡ቢ.ቢ.ሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.