Fana: At a Speed of Life!

10 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ተዘርፏል-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት አራት ወራት 10 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት መዘረፉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙንኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን÷ በአገሪቷ የተለያዩ አካባቢዎች በከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ዘረፋና ስርቆት መበራከቱን ገልጸዋል።
ከአሁን ቀደም ስርቆት ይስተዋልባቸው በነበሩ አካባቢዎች መጠኑ እየሰፋ እንዲሁም ከዚህ ቀደም ስርቆት በማይስተዋልባቸው አካባቢዎችም እየተስፋፋ መምጣቱን አስረድተዋል።
በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን የሀዋሳ ሻሸመኔ መስመር፣ ከአዋሽ አሰላ እንዲሁም በአማራ ክልል የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች መዘረፋቸውን ጠቁመዋል።
በዚህም በ2014 በጀት አመት አራት ወራት ውስጥ ብቻ 10 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት መዘረፉን አቶ ሞገስ ገልጸዋል።
የመሰረተ ልማት ስርቆቱን ተከትሎ የኃይል ተሸካሚ ማማዎችን አቅፈው የያዙትን ደጋፊ ብረቶች እንኳን ለመተካትን ለመጠገን ከዚህ በላይ ወጪ ይጠይቃል ነው ያሉት።
እንደ አቶ ሞገስ ገለፃ በኃይል ተሸካሚ ማማዎች ላይ ከ12 እስከ 141 ብረቶች በዘራፊዎች ተፈተው ተወስደዋል።
ስርቆት ፈፃሚዎቹ ህብረተሰቡ ትኩረቱን አገርን ማዳን ላይ ባደረገበት ወቅት ህዝብን ለችግር የሚዳርግና የህዝብን ንብረት የሚያጠፋ ድርጊት እየፈፀሙ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ከመቀሌ ዳሎል ሰመራ አፍዴራ፣ ከባህርዳር ወልዲያ ኮምቦልቻ የሃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በአዋሽ ወልዲያ ሐራ ገበያ የባቡር መስመር ላይ ጉዳት መድረሱንም ጠቅሰዋል።
ለፕሮጀክቶቹ ግብአት የሚሆኑ የተለያዩ ብረታብረቶች፣ ኮንዳክተሮች፣ ኢንሱሌተሮች መሰረቃቸውንና መሰባበራቸውንም እንዲሁም የግንባታ መሳሪያዎች ባሉበት እንዲበላሹና እንዲቃጠሉ መደረጉን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በእነዚህ አካባቢዎች ባሉ የፕሮጀክት መጋዘኖች ላይ ጭምር ዘረፋ የተፈፀመ መሆኑን ጠቅሰው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመጠበቅ ሂደት ህዝቡ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.