Fana: At a Speed of Life!

ለአገራችን ልንሰራው የሚገባን ብዙ በመሆኑ መበርታት አለብን – ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአገራችን ልንሰራው የሚገባን ብዙ በመሆኑ ይበልጥ መበርታት አለብን ስትል ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ጥሪ አስተላለፈች፡፡

ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲገቡ የተደረገውን ጥሪ ተቀብላ ዛሬ አዲስ አበባ ገብታለች፡፡

ጋዜጠኛዋ በዚህ ወቅት የበቃ ንቅናቄ ከኢትዮጰያ አልፎ በአለም መስፋፋቱ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ገልጻ ፥ እሷም ለአገሯ ይህን በማድረጓ ህልሟን እንዳሳካች እና ‘’የምንሰራው ብዙ ስላለ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊበረታ ይገባል’’ ስትል ጥሪ አቅርባለች።

ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ በተደረገላት አቀባበል ደስተኛ መሆኗን ገልጻ ፥ አገሬ በመገኘቴ ደስተኛ ነኝም ብላለች።

እናቷ ፕሮፌሰር ሃረገወይን አሰፋ በበኩላቸው ፥ በኢትዮጵያ አገሬ ተስፋ አለኝ ፤ እኔም ልጄም አገራችን በምትፈልገን ለማገልገል ዝግጁ ነን ብለዋል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.