Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ጽ/ቤት ምርጫውን ተከትሎ ባስተላለፈው መልዕክት በዓለም የግዙፉ ሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅት ኢትዮጵያ የቦርድ አባል ሆና መመረጧ በመላው ዓለም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ የተሻለ ሥራ እንዲከውን ኃላፊነቷን ትወጣለች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የድርጅቱ አስፈፃሚ ቦርድ የተቋሙ የበላይ አስተዳዳሪ ሲሆን፥ 36 የተመድ ወይም የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) አባል ሀገራትን የያዘ ነው።

ቦርዱ ለድርጅቱ ድጋፍንና የፖሊሲ አቅጣጫ የሚያደርግ ሲሆን፥ ስራውንም ይከታተላል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.