Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አሕመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ዋሺንግተን ዲሲ ገባ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 10 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አመታዊ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ዋሺንግተን ዲሲ ገባ።
ልዑኩ በቆይታው ከስብሰባው ባለፈ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ወገን ምክክር እንደሚያደርግ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ እና የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር እዮብ ተካልኝ ከገንዘብ ሚኒስትሩ ጋር ወደስፍራው አቅንተዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.