Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ህፃናት ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 27፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከወላይታ ሶዶ ከተማ ተነስተው ወደ አዲስ አበባ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 19 ህጻናትንና 6 አዘዋዋሪ ሴቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቋል።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ሸምሱ ሂክማ እንደገለፁት ህጻናቱን ማዳበሪያ በማልበስ አፍነው ሲያጓጉዟቸው የነበሩ ህፃናት እድሜያቸው ከ5 እስከ 10 እንደሚሆን ጠቁመዋል።
ህጻናቱ ወራቤ ከተማ ሲደርሱ ባሰሙት ጩኸት መነሻ ከህብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተከታትሎ ከተማ አስተዳደር ህጻናቱንና አዘዋዋሪ እናቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል።
ለህጻናቱ ምግብ በመስጠት ከአዘዋዋሪ ሴቶች ጭምር በፖሊስ በማጀብ ለወላይታ ፖሊስ ለማስረከብ ጉዞ መጀመሩንም ኢንስፔክተር ሸምሱ ጠቁመዋል።
አዘዋዋሪ እናቶች በሰጡት አስተያየት በዚህ እኩይ ተግባር ተሳታፊዎች ቁጥር በርካቶች መሆናቸውን ለፖሊስ በመግለጽ በጠዋቱ ክፍለጊዜ ህጻናትን የጫነ አንድ መኪና ወደ አዲስ አበባ መጓዙንም ተናግረዋል።
የሰላም ባለቤት የሆነው ህብረተሰብ መሰል የወንጀል ተግባራትን ከጸጥታው አካላት ጎን በመሆን ሊከላከል እንደሚገባም ኢንስፔክተሩ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡’
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.