Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለዓለም ምሳሌ የሚሆን የአረንጓዴ ልማትን እየተገበረች ነው -ዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ዕድገት ኢንስቲትዩት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማትን በምሳሌነት እያከናወኑ ካሉ ጥቂት ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን ዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ዕድገት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ገመዶ ዳሌ ተናገሩ።

መገናኛ ብዙኃን በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖና በአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ላይ ያላቸውን የዘገባ ሚና ለማጠናከር ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው።

የዓለም አቀፉ የአረንጓዴ ዕድገት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ገመዶ ዳሌ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማትን በምሳሌነት እያከናወኑ ካሉ ጥቂት ሀገራት አንዷ መሆኗን ጠቅሰው÷ ይህንንም ለዓለም በተግባር እያስመሰከረች ነው ብለዋል፡፡

በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ መድረኮች የአየር ንብረት ለውጥ ጫና ለመከላከል ርብርብ እንዲደረግ ግፊት ስታደርግ መቆየቷንም አውስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ በበኩላቸው÷ መገናኛ ብዙኃን የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎችን በዕውቀት ላይ ተመሥርተው መዘገብ ይገባቸዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የባለሙያዎችን የአዘጋገብ አቅም ለማሳደግና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ዘገባ እንዲያደርሱ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.