Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሩን በሲዳማ ክልል አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሩን ዛሬ በሲዳማ ክልል ወንዶ ገነት ወረዳ አስጀምሯል።

የትራስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ መርሐ ግብሩን በወረዳው በሚገኘው የወንዶገነት ዎሻ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ትምህርት ቤቶች አስጀምረዋል።

ሚኒስቴሩ የትምህርት ቤቶቹን የማስፋፊያ ግንባታ ስራዎችን ከወረዳው ተረክቦ እንደሚሰራም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

በተመሳሳይ ሚኒስቴሩ ከወንዶ ገነት ወረዳ አስተዳደር ጋር በጥምረት የሚያካሂደውን የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በዎሻ ቀበሌ ጀምሯል።

በመርሐ ገብሩ ላይ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት ሀኃላፊዎች፣የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሲዳማ ክልል የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብሩን ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በአለታ ወንዶ ከተማ ያስጀመረ ሲሆን ÷ከ567 ሺህ በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉበት መግለጹ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.