ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሁለት ሹመቶችን ሰጡ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሁለት ሹመቶችን ሰጥተዋል።
በዚህ መሰረትም ፦
1.ወይዘሮ ህይወት ሞሲሳ- የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር እና
2.ሜጀር ጀኔራል አህመድ ሀምዛ – የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል።
ሹመቱ ከመጋቢት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የተሰጠ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።