Fana: At a Speed of Life!

የታንዛኒያ የመንገደኞች አውሮፕላን ቪክቶሪያ ሐይቅ ላይ ተከሰከሰ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 49 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የታንዛኒያ የመንገደኞች አውሮፕላን ቪክቶሪያ ሐይቅ ላይ መከስከሱ ተሰማ፡፡

ከዳሬ ሰላም ወደ ቡኮባ ከተማ ሲጓዝ የነበረው አውሮፕላኑ አውሎ ንፋስ እና ከባድ ዝናብ እንዳጋጠመውና ይህም ለመከስከሱም ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም ከ49 ተሳፋሪዎች መካከል ከ20 በላይ የሚሆኑት መትረፋቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ነገር ግን እነዚህ መረጃዎች በይፋ አልተረጋገጡም ነው ያለው ቢቢሲ በዘገባው ።

የነፍስ አድን ሰራተኞች የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ርብርብ እያደረጉ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.