Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች በ10 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጎበኙ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ፥ በከተማዋ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና በሌሎች ዘርፎች ለህብረተሰቡ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ፕሮጀክቶች ግንባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም የኮልፌ መንዲዳ ሆስፒታልን ፣የላፍቶ ሆስፒታል ግንባታን ፣የኮልፌ እና ላፍቶ የገበያ ማዕከል ግንባታን ፣ ለአርሶአደር የልማት ተነሺዎች ማቋቋምያ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

ከነዚህ በተጨማሪም በበመዲናዋ የመጀመሪያ የሆነውንና ለስራ እድል ፈጠራ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የኢንዱስትሪ ክላስተር ፕሮጀክቶች መመልከታቸውንም ነው ያነሱት፡፡

ፕሮጄክቶቹ በአጠቃላይ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው እየተገነቡ የሚገኙ ሲሆን ፥ አብዛኛው አፈፃፀማቸው ጥሩና ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በዚህም በልዩ ትኩረት እየተሰሩ እንዳሉም መገምገማቸውንም ነው የተናገሩት።

አክለውም ፥ በሆስፒታሎች ግንባታ ላይ የሚታየዉን መጓተት በፍጥነት መስተካከል እንዳለበት ከኮትራክተሮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገን ችግሩን ለመፍታት ተስማምተናልም ብለዋል ከንቲባዋ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.