Fana: At a Speed of Life!

የፈረንሳይና የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሚቀጥለው ሣምንት ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎ እና የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ቤርቦክ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ተገለጸ፡፡

ሚኒስትሮቹ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተፈረመውን ስምምነት ተከትሎ የሰላም ሂደቱን ለማጠናከር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዙ ነው ያስታወቁት።

“በሚቀጥለው ሣምንት ከስራ ባልደረባዬ አናሌና ቤርቦክ ጋር ወደ ኢትዮጵያ እሄዳለሁ” ሲሉ ኮሎና ለኤልሲአይ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የአፍሪካ ህብረት እርምጃና የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለመደገፍ ወደ ኢትዮጵያ ከአቻቸው ጋር እንደሚያመሩም ነው የገለጹት፡፡

የሁለቱ ሚኒስትሮች ጉብኝትም ጥር 4 እና 5 እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም በምግብ ዋስትና፣ በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት ግንኙነት፣ በአውሮፓ ህብረት እና በአፍሪካ ህብረት ግንኙነት ላይ እንደሚመክሩም ኤኤፍፒ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.