አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ2023ቱ የለንደን ማራቶን ይሳተፋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በቀጣይ ሚያዚያ ወር ላይ በሚካሄደው የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፍ ተገለፀ፡፡
ቀነኒሳ በቀለ በበርሊን ማራቶን 2 ሰአት ከ1 ሰከንድ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በማራቶን ታሪክ ሁለተኛው የፈጣን ሰዓት ባለቤት መሆኑ ይታወቃል ።
የሦስት ጊዜ የኦሊምፒክ ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ግማሽ ማራቶን 1 ሰዓት ከ22 ደቂቃ በመግባት ቀደም ብሎ በእንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ ተይዞ የነበረውን የለንደን ማራቶን ክብረ ወሰን ማሻሻሉ ይታወሳል።
ሞስነት ገረመው ፣ ብርሀኑ ለገሰ እና ልዑል ገብረስላሴ በውድድሩ ኢትዮጵያን ሚወክሉ አትሌቶች ናቸው ተብሏል።
የ2022 የለንደን ማራቶን አሸናፊው ኬኒያዊው አሞስ ኪፕሩቶ እና እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ በዚህ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ መባሉን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡