Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት ትብብር እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የ180 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ የያዘውን የ2023-2025 የኢትዮጵያ እና የጣልያን የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።
 
የፋይናንስ ስምምነቱ በኢኮኖሚ ልማት በተለይ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች እና በጤና እና በትምህርት መሠረታዊ አገልግሎት አቅርቦት፣ ቁልፍ በሆኑ ተግባራት ላይ እንደሚውል ተገልጿል፡፡
 
ስምምነቱ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም እና የአሥር ዓመት የልማት ዕቅድን ለማስቀጠል የሚደግፍ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
 
ሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነትን በመግለጽ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ስብሰባቸውን ማጠናቀቃቸው ተመላክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.