Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ምስጋኑ ለፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች  ጋር ገለፃ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ለፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ገለፃ አደረጉ።

ሚኒስቴር ዴኤታው በሃገራቱ ወቅታዊ ቀጣይ በሆኑ የግንኙት ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ነው ገለፃ ያደረጉት።

በገለፃው ላይ በንግድ እና ቢዝነስ ዘርፍ እየታየ ያለው አበረታች ግንኙነት በፓለቲካ ዘርፍ በተመሳሳይ ሊደገፍ እንደሚገባ አምባሳደር ምስጋኑ አስገንዝበዋል ።

ኢትዮጵያ በምጣኔ ሃብት ረገድ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ አዳጊ ሃገራት አንዷ እንደሆነች ያብራሩት አምባሳደር ምስጋኑ፥ የፓኪስታን ባለሃብቶች ተሳትፏቸውን ይበልጥ እንዲያሳድጉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የሃገራቱን ግንኙነት በሁለትዮሽ የፓለቲካ ምክክር እና በጋራ ሚኒስትሮች ደረጃ እንዲጠናከር አምባሳደር ምስጋኑ ጥሪ አቅርበዋል።

በምክክሩ ላይ ቀጠናዊ እና ሃገራዊ በሆኑ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይም ገለፃ ተደርጎል።

የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ኢትዮጵያ በኢስላማባድ ኤንምባሲዋን በመክፈቷ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ትብብር ማሳደግ ፓኪስታን ከአፍሪካ ጋር ጭምር ለሚኖራት ግንኙነት እድገት ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.