Fana: At a Speed of Life!

በመጪዎቹ ሳምንታት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጪዎቹ ሳምንታት ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚጠበቅ የምስራቅ አፍሪካ የአየር ንብረት የልህቀት ማዕከል አስታወቀ።

በተለይም በአብዛኛዎቹ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሰሜን ምዕራብ ደቡብ ሱዳን አካባቢዎች ከ 200 ሚሊ ሜትር በላይ የሆነ ከባድ ዝናብ እንደሚጠበቅ ማዕከሉ አሳስቧል።

በደቡባዊ ሱዳን፣ በምእራብ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በምዕራባዊ ኤርትራ፣ በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ፣ በምዕራብ እና ማዕከላዊ ደቡብ ሱዳን፣ በሰሜን ኡጋንዳ አንዳንድ ክፍሎች እና በምዕራብ ኬንያ ደግሞ ከ50-200 ሚሊ ሜትር የሆነ መካከለኛ ዝናብ ይጠበቃል ተብሏል።

እንዲሁም በማዕከላዊ ሱዳን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በጅቡቲ፣ በደቡባዊ ኤርትራ፣ በሰሜን እና በደቡባዊ ሶማሊያ፣ በምዕራብ ኬንያ፣ በማዕከላዊ እና በደቡባዊ ኡጋንዳ እንዲሁም በምስራቅና ደቡብ ታንዛኒያ አንዳንድ ክፍሎች ላይ ከ50 ሚሊ ሜትር በታች የሆነ ቀላል ዝናብ ይጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

በአብዛኞቹ ታንዛኒያ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ አብዛኛው የምሥራቅና የሰሜን ኬንያ፣ የመካከለኛው ሶማሊያ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ አንዳንድ ክፍሎች፣ደቡብ ምስራቅ ደቡብ ሱዳን እና ሰሜን ሱዳን ውስጥ ደረቃማ የአየር ሁኔታ ይጠበቃል።

በሰሜን ምስራቅ እና ምዕራብ ኢትዮጵያ፣በሱዳን ማዕከላዊ እና ደቡባዊ ክፍሎች ፣በኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበር ተሻጋሪ አካባቢዎች፣በሰሜን-ምዕራብ ደቡብ ሱዳን እና በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ በጣም ከባድ ዝናብ ይጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የሙቀት መጠን በተመለከተ በሰሜን ሱዳን፣ በኤርትራ፣ በሰሜን-ምስራቅ ኢትዮጵያ አንዳንድ ክፍሎች፣ በጅቡቲ ክፍሎች እና በሶማሊያ ሰሜን-ምዕራብ ጠረፍ ባሉ ክልሎች ከ32℃ (ዲግሪ ስንት ግሬድ) በላይ ከፍተኛ ሙቀት ይጠበቃል።

በምስራቅ ኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምስራቅ ኬንያ፣ በሰሜን ኡጋንዳ፣ በምስራቅ ሩዋንዳ እና በቡሩንዲ እንዲሁም በምዕራብ እና ምስራቅ ታንዛኒያ
መካከለኛ የሙቀት መጠን ከ20 እስከ 32 ዲግሪ ስንት ግሬድይጠበቃል።

ከደቡብ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ፣ ከማዕከላዊ እስከ ምዕራብ ኬንያ ክፍሎች ከደቡባዊ ኡጋንዳ፣ ከምዕራብ ሩዋንዳ፣ ከምዕራብ ቡሩንዲ እና ከመካከለኛው እስከ ደቡባዊ ታንዛኒያ ክፍሎች ከ 20℃ (ዲግሪ ስንት ግሬድ) በታች የሆነ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.