Fana: At a Speed of Life!

ትራምፕና ባይደን የመጨረሻ ፕሬዚዳንታዊ ክርክር አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የመጨረሻውን የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ክርክር አካሂደዋል፡፡

ሌሊት በተካሄደው ክርክር የኮሮና ቫይረስ፣ የአየርንብረት እና በዘር ላይ ያተኮሩ ጉዳዮች መድረኩን ተቆጣጥረውት ነበር፡፡

በክርክራቸው ትራምፕ ተጨባጭ መረጃ በሌለው ጉዳይ ባይደንን ተናግረዋል ነው የተባለው፡፡

ይህም ባይደን ልጃቸው ከሩሲያ ጋር ባደረገው የንግድ ስምምነት በግል ተጠቅመዋል ሲሉ ተችተዋቸዋል፡፡

ባይደን በአንጻሩ የትራምፕን የግብር ጉዳይ እና የባንክ ደብተር ጉዳይ አንስተዋል፡፡

ትራምፕም ለዚህ ጉዳይ ነጋዴ ነበርኩ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ባይደን የኮሮና ቫይረስን አንስተው ወደ ከፋው ጊዜ ልንገባ እንችላለን በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡

በዚህም 220 ሺህ አሜሪካውያንን ህይወት ለቀጠፈው የኮሮና ቫይረስ ትራምፕን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

ከ11 ቀናት በታች በቀሩት በ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ባይደን እየመሩ መሆኑ ተነግሯል፡፡

እስካሁን ድረስ ከ47 ሚሊየን በላይ ዜጎች መምረጣቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ባይደንና ትራምፕ የመጀመሪያ ክርክራቸውን ከ23 ቀናት በፊት ያካሄዱ ሲሆን በዘለፋ የተሞላ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ሁለተኛ ክርክራቸው ደግሞ ቀጠሮ ተይዞለት ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ በመያዛቸው ምክንያት በቨርችዋል እንዲካሄድ ቢወሰንም በመጨረሻ ሰዓት ፕሬዚዳንቱ ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ይታወቃል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.