Fana: At a Speed of Life!

የጋራ ታሪካዊ ምዕራፍ እናክብር በሚል መሪ ቃል ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ የእራት ግብዣ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ላደረጉት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የጋራ ታሪካዊ ምዕራፍ እናክብር በሚል መሪ ቃል የእራት ግብዣ ተካሄደ፡፡

የእራት ግብዣው ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፊሪያት ካሚል፣ የሀይማኖት መሪዎችና የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በብሄራዊ ቤተ መንግስት ተከናውኗል።

ግብዣው ኢትዮጵያና ኤርትራ ለሁለት አስርት ዓመታት የነበረባቸውን ልዩነት በመፍታት ግንኙነታቸውን ማደሳቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኖቤል የሰላም ሽልማት ካገኙ በኋላ መካሄዱ ልዩ ያደርገዋል ተብሏል።

በእራት ግብዣው ላይ የሁለቱን ሀገራት የእርስ በእርስ ግንኙነት የሚያጠናክሩ የኪነ ጥበብ ስራዎች ቀርበዋል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.