Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) – ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ።

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትም የሆኑት ዶ/ር አብራሃም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ።

ዶ∕ር አብርሃም በተለያዩ የመንግስት ሃላፊነቶች ላይም አገልግለዋል::

በሃላፊነት ካገለገሉባቸው ተቋማት ውስጥ የኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ፣ ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የድሮ ሜቴክ ፣ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ፣ የአምቦ ዩንቨርስቲን በቦርድ ሰብሳቢነት ፤ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ አባል በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የህዳሴውን ግድብ ከውድቀት በማዳን ውሰጥ ቁልፍ ሚና እንደተጫወቱ የነገርላቸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.