Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡
በውይይታቸው በኢትዮጵያና በቱርክ ሁለትዮሽ ግንኙነትንና ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የቱርክ ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት በትዊተር ገፁ አስፍሯል፡፡
በዚህ ወቅት የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን ቱርክ ለኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ አፅንዖት የሰጡ ሲሆን ÷ሃገሪቱ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.