Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የአማራ ተወላጅ ባለሀብቶች በአሸባሪው ትህነግ ተፈናቅለው ደሴ ለሚገኙ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ የአማራ ተወላጅ ባለሀብቶች በአሸባሪው ትህነግ ተፈናቅለው ደሴ ለሚገኙ ዜጎች የአንድ ወር የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ባለሀብቶቹ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻም ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በተወካዮቻቸው አቶ በላይነህ ክንዴና አቶ ደስታ ምህረቴ አማካኝነት ነው ድጋፉን ያበረከቱት፡፡

የባለሀብቶቹ ተወካይ አቶ በላይነህ ክንዴ ከጸረ ኢትዮጵያ ኀይሎች ጋር በመተባበር የአማራን ሕዝብ ለማጥፋትና ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳው አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን እስኪጠፋ ባለሀብቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ሌሎች ባለሀብቶችም ሀገሪቱ እየገጠማት ያለውን ውስብስብ ችግር ለመፍታት መሰል ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ የአማራ ውኃ ሥራ ተቋራጮች ማኅበር በደባርቅና በደብረዘቢጥ ግንባር ለሚገኘው ለመከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ለሚሊሻ እና ፋኖ 1 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የስንቅ እና ሌሎች ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የአማራ ውኃ ሥራ ተቋራጮች ማኅበር ጸሐፊ ኀይሉ አበጀ ሀገርን ለማዳን ሁሉም በሕልውና ዘመቻው ላይ መረባረብ አለበት ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.