Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ቀንን አራዘመ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ ቀንን እስከ መስከረም 2 ቀን 2014 ዓ.ም አራዘመ፡፡

ቦርዱ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ድምፅ ለሚሰጥባቸው የምርጫ ክልሎች ማለትም በሃረሪ ክልል፣ በሶማሌ ክልል የተወሰኑ ምርጫ ክልሎች እና በደቡብ ክልል ምእራብ ኦሞ ዞን የመራጮች ምዝገባን ሲያከናውን መቆየቱ እና የምዝገባው እለትም ዛሬ ጷግሜ 5 ቀን እንደሚጠናቀቅ ይታወሳል።

ሆኖም በተለያዩ ቦታዎች ለመመዝገብ ፈልገው እድሉን ያላገኙ ዜጎችን ለማካተት ሲባል ምዝገባው መስከረም 2 ቀን 2014 አ.ም እሁድ እንዲከናወን ወስኗል፡፡

የመራጮች ምዝገባ የመጨረሻ ቀንም መስከረም 2 ቀን 2014 መሆኑን በመገንዘብ የፓለቲካ ፓርቲዎች፣ የመራጮች ትምህርት ሰጪዎች እና ሚዲያዎች ዜጎች ተጨማሪውን ቀን ተጠቅመው እንዲመዘገቡ እንዲያበረታቱ ቦርዱ ጠይቋል፡፡

የምርጫ አስፈጻሚዎችም በተጨመረው አንድ ቀን የመራጮች ምዝገባን በምርጫ ጣቢያው ተገኝተው እንዲያከናውኑ ማሳሰቡን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.