Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ አቅመ ደካሞችንና የስጋ ደዌ ተጠቂዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ በአዲስ አበባ አለርት ሆስፒታል አካባቢ የሚኖሩ አቅመ ደካሞችና የስጋ ደዌ ተጠቂዎችን ጎበኙ፡፡
አዲስ አመት በአልን ምክንያት በማደርግ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ አቅመ ደካሞችንና በስጋ ደዌ የተጠቁ የማህበረሰብ አባላትን አለርት ሆስፒታል አካባቢ በመገኘት እንኳን አደረሳቹ ብለዋል።
በነፍስ ወከፍም ለ100 የስጋ ደዌ ተጠቂዎች 1000 ብር ድጋፍ እና የብርድ ልብስ ስጦታ አበርክተዋል፡፡
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ አዲሱን አመት ስናከብር ረዳት የሌላቸዉ የተረሱ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማስታወስ ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት ፡፡
ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ አዲሱ አመት የሰላም የአንድነት የይቅርታና የመደጋገፍ እንዲሆን መመኘታቸውን ከቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
0
People Reached
145
Engagements
Boost Post
135
4 Comments
6 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.