Fana: At a Speed of Life!

የውሀ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጥቃት ለወደሙ መሰረተ ልማቶች ጥገና የሚውል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሀ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ጥቃት ለወደሙ የውሀና የሀይል አገልግሎት መሰረተ ልማት ጥገና የሚውል የ20 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን ለክልሉ ርዕሠ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ያስረከቡት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በወረራው ለዜጎች የውሀ እና የሀይል አገልግሎት የሚሠጡ ተቋማት ወድመዋል፤ በዚህም ዜጎች ችግር ገጥሟቸዋል ብለዋል።

ለዚህ ችግር የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ መስጠት በማስፈለጉ ተቋሙ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው “በወረራው የሀይል አቅርቦት ሠጭ ተቋማት ተጎድተዋል፤ በዚህም ሀይል ተቋርጧል፣ ተስተጓጉሏል” ብለዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች የሀይል ማስተላለፊያ ገመዶችና ቁሳቁስ በዝርፊያ በመወሠዳቸው ጥገናው ከፍተኛ ስራ የሚጠይቅ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለዚህም ነፃ ለወጡ አካባቢዎች ቅድሚያ በመስጠት ጥናቶች እየተካሄዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው በዚህ ወቅት የትኛውም ዓይነት ድጋፍ ልዩ ትርጉም የሚሠጠው ነው ያሉ ሲሆን በየከተሞች የውሀ ተቋማት በመዘረፋቸውና በተፈናቃዮች ምክንያት ተጨማሪ ጫና በመፈጠሩ ነዋሪዎች ለንፁህ የመጠጥ ውሀ ችግር ተዳርገዋል ብለዋል ፡፡

ከተከዜ ማመንጫ ሀይል ያገኙ በነበሩ አካባቢዎች ሀይል ሲቋረጥ የውሀ አገልግሎቱም አብሮ መቋረጡንም ጠቅሰውም በዚህ ምክንያት ነዋሪዎች የጤና ችግር እየገጠማቸው መሆኑን በመግለፅ ድጋፉ በየደረጃው ችግሩን ለመቅረፍ ያግዛል ብለዋል፡፡

በዘንድሮው በጀት ዓመት የመስኖ ልማት፣ የመጠጥ ውሀ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማዳረስ የተያዘው በጀት ለጦርነት እየዋለ በመሆኑ ክልሉ በልማት ወደ ኋላ እንዳይቀር የሁሉም አካላት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አቶ አገኘሁ ማሳሰባቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.