Fana: At a Speed of Life!

የተከማቹ የመልካም አስተዳድር ችግሮችን መቅረፍ የክልሉ መንግስት ቀዳሚ ሥራ ነው – አቶ ርስቱ ይርዳው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን ሉዓላዊነት ከማስከበር ጎን ለጎን የክልሉ መንግስት የህዝቡን ጥያቄዎች ለመፍታት በተያዘው ዓመት እንደሚሰራ የደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ገለጹ፡፡
ህወሓት በደቡብ ክልል የግጭት ማዕከል ለማድረግ ባደረገው ሙከራ የሰላምና ደንህነት ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች ከህዝቡ ጋር በመሆን እርቀ ሰላም የማስፈን ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡
የአርብቶ እና አርሶ አደሮችን ኑሮ ለማሻሻልም የኩታ ገጠም እርሻ በዘመናዊ መሳሪያዎች ታግዞ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡
የአደረጃጃት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ እየመለሱ መሄድና የህዝብ ውሳኔ የተላለፈበት 11 ክልል የማቋቋም ድጋፍ እንደሚደርጉም አረጋግጠዋል፡፡
ሌብነትን ለማስቀረት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር እንደሚዘረጋ ጠቁመው÷ በሌብነት ተሰማርተው የሚገኙ ግለሰቦች ላይም በመረጃ የተደገፈ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡
ስራ አጥነት ለመቀነስም የተለያዩ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ ለመቀነስ ይሰራል ነው ያሉት ርዕሠ መስተዳድር አቶ ርሰቱ ይርዳው።
በበላይ ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.