Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል የሚሊሻ አባላት ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በብርቆድ ወረዳ በሻለቃ ከደር መሀመድ የውትድርና ማሰልጠኛ ማዕከል ሲሰለጥኑ የነበሩ የሚሊሻ አባላት ተመረቁ፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ መሀመድ አሊ፣የክልሉ የልዩ ሃይል ዋና አዛዥ ም/ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ፣የክልሉ ሚሊሻ ኃይል አቶ አብዱላሂ ቃሲምና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በሥነ ስርአቱ ላይ አቶ መሀመድ አሊ ለፀጥታው ዘርፍ በክልሉ በተሰጠው ትኩረት የሚሊሻ አባላት መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

የሶማሌ ክልል መንግስት በክልሉ ለሰፈነው ሰላም ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን ገልፀው በቀጣይም ይህንኑ የማጠናከር ስራዎችን እንደሚያከናውን አረጋግጠዋል።

ረ/ኮሚሽነር መሀመድ አህመድ በበኩላቸው የሶማሌ ክልል የፀጥታ ሀይል የሀገሪቱን ዳር ድንበርና የክልሉን ሰላም በማረጋገጥ ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ እየተወጣ መሆኑን አንስተው ከዚህም ባለፈ አሸባሪውን የህወሓት ጁንታ ቡድን ግብአት መሬት ለማረጋገጥ የክልሉ የፀጥታ ሀይል ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉ የሚሊሻ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱላሂ ቃሲም በክልሉ ከመጣው ለውጥ በኋላ በተሰራው መዋቅር ለሚሊሻ አባላት ትኩረት በመስጠት መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ትልቅ ስራ መሰራት መቻሉን አንስተዋል።

ተመራቂ የሚሊሻ አባላቱም የክልሉን ሰላም በማጠናከር የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀው አሸባሪውን የህወሓት ጁንታ እንደ ሀገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር በሚደረገው ትግል የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን መናገራቸውን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል ።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.