Fana: At a Speed of Life!

ወርልድ ቪዥን በአሸባሪው ህወሓት ለተፈናቀሉ ወገኖች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወርልድ ቪዥን 2 ሚሊየን 48 ሺህ ብር የሚገመት የመጠጥና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በሰሜን ጎንደር ዞን በአሸባሪው ህወሓት ለተፈናቀሉ 1 ሺህ 500 ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።
የወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ፕሮጀክት የደንቢያና አካባቢው ፕሮጀክት ሥራ አሥኪያጅ አቶ ዮናስ አትክልት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚያስተባብሩ ሲሆን በተፈናቃዮች በኩል ያለውን ችግር በማጥናት መደገፍ መቻላቸውን ገልጸዋል።
ድርጅቱ ሁሉንም አካባቢ በእኩል የሚያገለግል ሲሆን በገንዘብና በጊዜ ተደራሽ እናደርጋለን ብለዋል።
አሁን በጊዜያዊነት በመጠለያ ጣቢያ ያሉትን የመደገፍ ሥራ እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው፥ የክልሉ መንግስት በሚያወጣው የመልሶ ማቋቋም ፕሮፖዛል መሠረት እንደ ድርጅቱ የበጀት መጠን እየታየ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ተናግረዋል።
የምዕራብ ጠለምት ዲማ ወረዳ ተፈናቃይ ወይዘሮ ሲሣይ ሙሉ ወርልድ ቪዥን የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ እንዳደረገላቸው መግለጻቸውን ከሰሜን ጎንደር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
0
People reached
35
Engagements
Boost post
34
1 Share
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.