Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፍ የአደገኛ እፅ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መነሻቸውን ብራዚል ሳኦፖሎ መዳረሻቸውን ደግሞ ዱባይና ናይጄሪያ በማድረግ በአውሮፕላን ሲጓዙ የነበሩ የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
የአደገኛ ዕፅ አዘዋዋሪዎቹ ሁለት ናይጄሪያውያንና አንዲት ብራዚላዊት ሲሆኑ፥ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገው ፍተሻ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል፡፡
ግለሰቦቹ አደገኛ ዕፁን በውስጣዊ የሻንጣ አካል በመደበቅና ውጠው በሆዳቸው በመያዝ ለማሳለፍ ሙከራ ቢያደርጉም የፌደራል ፖሊስ አባላት ባደረጉት የተጠናከረ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል፡፡
በብራዚላዊቷ ላይ በተደረገ ፍተሻ ከ13 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን 666 ጥቅል ፍሬና በዱቄት መልክ የተዘጋጀ ከ17 ኪሎግራም በላይ የሚመዝን 11 እሽግ ኮኬይን የተሰኘ አደገኛ ዕፅ በሻንጣዋ ይዛ መገኘቷ ተረጋግጧል፡፡
ሁለቱ ናይጄሪያዊያን አደገኛ ዕፁን በሆዳቸው ይዘው ሊያዘዋውሩ እንደሚችሉ በመጠራጠር በፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል በተደረገላቸው የኤክስ ሬይ ምርመራ የተገኘባቸው ሲሆን 1 ሺህ 650 ግራም የሚመዝን 83 ፍሬ ኮኬይን ከሆዳቸው እንዲወጣ መደረጉ ተገልጿል፡፡
ግለሰቦቹም በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.