Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዢ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዢ ሼክ መሀመድ ቢን ረሺድ አልመክቱም ጋር ተወያዩ።

ውይይቱ በዱባይ እና በመላው ዓረብ ኢሚሬቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያነሷቸውን ጥያቄዎች መመለስ እና መፍታት በሚቻልበት አግባብ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ሼክ መሀመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያን ለመለወጥ የሚያደርጉትን ጥረት እንዲሁም፥ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ሰላም ለማስፈን የሚያከናውኑትን ሥራ እንደሚያደንቁና እንደሚደግፉ ገልፀውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም በትናንትናው ዕለት 300 ከሚሆኑ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ተወካዮች እና አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት የቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ለሼክ መሀመድ ቢን ረሺድ አንስተውላቸዋል።

ሼክ መሀመድ በኢትዮጵያውያን የስራ ፈቃድ፣ የአምልኮ እና የትምህርት ቤት ግንባታ ቦታዎችን በተመለከተ በቀረቡ ጥያቄዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ከልዩ ልዩ የስራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩበት ቃል ገብተዋል።

በአቡዳቢም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ የሚሆን ቦታ መፍቀዳቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.