Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ፣ የካማሺ ዞን አመራሮች እና የደብረ ማርቆስ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች የዘማች አርሶ አደር ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ።
 
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች “ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት” ዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በዛሬው ዕለት በመሰብሰብ ደጀንነታቸውን አሳይተዋል፡፡
 
ሰራተኞቹ ለገጣፎ ለገዳዲ አካባቢ በመገኘት ነው የዘማች አርሶ አደር ቤተሰቦችን የደረሰ ሰብል የሰበሰቡት፡፡
 
በተመመሳሳይ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ የተመራ ልዑክ በካማሺ ዞን ሄና ቀበሌ የሚገኙ የዘመች ቤተሰቦችን ሰብል ሰብስቧል፡፡
 
በመርሃ ግብሩ የዞን ፣ የካማሺ ከተማና የካማሺ ወረዳ አመራሮች፣ የየሰከቴር መስሪያ ቤት የመንግስት ሠረተኞች እንዲሁም የካማሺ ከተማ ነዋሪዎች መሳተፋቸውን ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የደብረ ማርቆስ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞችም እንዲሁ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የዘማች አርሶ አደር ቤተሰቦችን እና የአቅመ ደካማ ወገኖችን ሰብል ሰብስበዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.