Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በሲሪንቃ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ባደረሰው ቃጠሎ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት ወድሟል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው ሲሪንቃ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ላይ ባደረሰው ቃጠሎ ከ2 ቢሊየን ብር በላይ ሀብት መውደሙን ኢንስቲቲዩቱ ገለጸ፡፡
የሲሪንቃ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ አማራ በምርምር የታገዙ የግብርና ምርቶችን በማቅረብ ለዜጎች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ድርጅት ነው፡፡
የክልሉን ሕዝብ በኢኮኖሚ ለማድቀቅ ቆርጦ የተነሳው የሽብር ቡድኑ የአርሶ አደሮችን የልማት ተጠቃሚነት ለመጉዳት የምርምር ማዕከሉን ሙሉ በሙሉ በእሳት አቃጥሎ መሄዱን አሚኮ ዘግቧል፡፡
በሲሪንቃ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት ተመራማሪ እና የኢንስቲቲዩቱ ተወካይ ኃላፊ አካሉ ገብሩ እንደገለፁት÷ የሲሪንቃ ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት በምርምር የታገዙ የግብርና ውጤቶችን ለአርሶ አደሮች በማቅረብ ተጠቃሚነታቸውን ሲያረጋግጥ ቆይቷል።
ማዕከሉ በተለይም ለአርሶ አደሮች የመነሻ ዘር ብዜትን በማቅረብ፣ በእንስሳት እና በደን ልማት በምርምር የታገዙ ሥራዎችን በማውጣት ከፍተኛ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
አሸባሪውና ወራሪው ቡድን ግን የምሥራቅ አማራን የልማት ተጠቃሚነት ለማደናቀፍ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን ኢንስቲቲዩት ሙሉ በሙሉ በእሳት አቃጥሎ ሂዷል ነው ያሉት፡፡
የሽብር ቡድኑ የተቋሙን እንስሳት፣ 32 ሕንጻዎችን፣ የበለፀጉ የምርምር ውጤቶችን እና ሥራዎችን አቃጥሎ መሄዱን ተናግረዋል።
በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ከተቋሙ የወደመው ሀብት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚገመት አቶ አካሉ ተናረዋል፡፡
በኢንስቲቲዩቱ በተመራማሪነት እና በክፍል ኃላፊነት ሲሠሩ የነበሩ የአሸባሪው ቡድን ተላላኪዎች በውድመቱ መሳተፋቸው የሚያሳዝን ድርጊት ነው ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.