Fana: At a Speed of Life!

በገለኣሉ ወረዳ የአዋሽ ወንዝ በባለፈው ክረምት የሰበረበት ቦታ እና ገዋኔ አካባቢ የአዋሽ ወንዝ የፍሰት ሁኔታ ተጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ እና የተለያዩ አመራሮች በገለኣሉ ወረዳ የአዋሽ ወንዝ በባለፈው ክረምት የሰበረበትን ቦታ እና ገዋኔ አካባቢ የአዋሽ ወንዝ የፍሰት ሁኔታን ጎበኙ፡፡

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ ፣ የውሀ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሱልጣን ወሊ እና የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ናቸው በገለኣሉ ወረዳ የአዋሽ ወንዝ በባለፈው ክረምት የሰበረበትን ቦታ እና ገዋኔ አካባቢ የአዋሽ ወንዝ የፍሰት ሁኔታን የጎበኙት፡፡

በተጨማሪም አመራሮቹ በአዋሽ ወንዝ ነባራዊ ሁኔታ እና በተፋሰስ ልማት ጉዳዮች ላይ በአዋሽ 7 ከተማ ተወያይተዋል፡፡

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ በቀጣይ የወንዙ የተጎዱ አካባቢዎች በአፋጣኝ ተጠግነው ወደ ስንዴው ልማት እንዲገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

በአሊ ሹምባሪ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.