Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጥምቀትን በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ እንዲያከብሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዳያስፖራዎች እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የጥምቀት በዓልን በጎንደር እንዲያከብሩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ጥሪ አቀረቡ፡፡
 
ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ÷በጎንደር ከተማ የጥምቀትን በዓልን ለማክበር ሁሉም ከውጭ የሚገቡም ሆኑ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲታደሙ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪ ማቅረቧን አስረድተዋል፡፡
 
ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የተጎዱ ወገኖችን መደገፍ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ በበኩላቸው÷በጥምቀት በዓል ልዩ ልዩ ዝግጅቶች የተካተቱበት የባሕል ሳምንት እንደሚካሄድ መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
 
በጥምቀት በዓል የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ (ሹሩባ) በክብር ወደ ጎንደር ከተማ የሚገባ መሆኑን ከንቲባው ገልጸው÷ይህንን ታሪካዊ ኹነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ጎንደር በመገኘት መታደም እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.