Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ተቋርጦ የነበረው የመደበኛ የመንግስት ስራ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው መደበኛ የመንግስት ስራ ከነገ ማክሰኞ ታህሳስ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀመር የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ መሀመድ አህመድ አሊ በሰጡት መግለጫ÷የህወሓት ቡድን በክልሉ ባደረገው ወረራ ባስከተለው ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ምክንያት የክልሉ የመንግስት ስራ ተቋርጦ መቆየቱን አንስተዋል፡፡
የአፋር ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻ እና የአፋር ህዝባዊ ሀይል ከጀግናው መከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ባደረጉት ተጋድሎ ወራሪውን ሀይል ደምስሰዋል ብለዋል፡፡
ስለሆነም የክልሉ መደበኛ የመንግስት ስራ ከነገ ማክሰኞ ታህሳስ 19 ቀን 2014 ዓ.ም በአጠቃላይ በክልሉ ሙሉ እንዲጀመር እና የመንግስት ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ እንዲገኙ የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጥሪ አቅርቧል ሲል የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.