Fana: At a Speed of Life!

በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የነዳጅ መያዣ ውስጥ ቁርጥራጭ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የነዳጅ መያዣ (ታንከር) ውስጥ ቁርጥራጭ ቁሳቁሶች ተገኙ።

ቁርጥራጮቹ የተገኙት ለተለያዩ አየር መንገዶች ሊሰጡ በተዘጋጁ አዳዲስ የኩባንያው ምርቶች ላይ ነው ተብሏል።

ሁኔታው በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ላይ ይነሳ የነበረውን የደህንነት ስጋት ከፍ አድርጎታል ነው የተባለው።

የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ፕሮግራም ክፍል ሃላፊ ሁኔታው ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ተናግረዋል።

ይሁን እንጅ ተገኘ የተባለው ቁርጥራጭ ቁሳቁስ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ለተጨማሪ ምርመራና ጥገና በሚል ከበረራ የሚያግድ አይደለም ብለዋል።

ኩባንያው በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ምርመራና ማጣራት እንደሚያደርግ ገልጿል።

የአሜሪካ አቪየሽን ባለስልጣን ደግሞ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የኩባንያውን ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን አስታውቋል።

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከዚህ ቀደም በተከሰቱ ሁለት አደጋዎች ከ240 በላይ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይታወሳል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ባለፈው አመት መጋቢት ወር ላይ በረራ ማቋረጡ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.