Fana: At a Speed of Life!

በዳያስፖራ አባላትና በሀገር ውስጥ ቡድኖች መካከል የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዳያስፖራና በሀገር ውስጥ ቡድኖች መካከል “ስፖርታችን ለአብሮነታችን” በሚል መሪ ሀሳብ የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ ተካሄደ፡፡
የቀድሞ የብሔራዊ ቡድንና የክለብ ተጫዋቾች የነበሩ ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት በተመለሱ የዳያስፖራ ቡድኖች እና በሀገር ቤት ቡድኖች መካከል በተካሄደው የወዳጅነት የእግር ኳስ ጨዋታ 36 ተጫዋቾች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡
አስቀድሞ በተካሄደው የኮሜዲያንና የእግር ኳስ ደጋፊዎች ግጥሚያ ደግሞ 32 ተጫዋቾች ተሳትፈዋልም ነው የተባለው።
ስፖርት ዓለምአቀፋዊ ቋንቋ መሆኑን የገለጹት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሐመድ እንድሪስ ለአሸናፊ ቡድኖች ሽልማት አበርክተዋል፡፡
የውድድሩ ዓላማ ወዳጅነትን ማጠናከር መሆኑን ገልጸው÷ ዳያስፓራው ስፖርትን ለእርስ በእርስ ትስስር ሊጠቀምበት እንደሚችል እና በስፖርታዊ ውድድር ውስጥ ማሸነፍና መሸነፍ ሊኖር እንደሚችልም ጠቅሰዋል፡፡
ዳያስፖራው አመቱን በሙሉ በግልም ሆነ በተናጠል ወደ ሀገር ቤት በመምጣት የተጀመሩ ስራዎችን መደገፍ እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል፡፡
ስፖርት ዳያስፖራውንና በሀገር ቤት ያለውን ማህበረሰብ ትስስር ለማጠናከር ትልቅ ድርሻ እንዳለው በጨዋታው የተሳተፉ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ተናግረዋል፡፡
በወዳጅነት ጨዋታው ላይ ለተሳተፉ የሜዳሊያ ሽልማት፣ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቡድኖች የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማቶች እንዲሁም ልዩ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የማስታወሻ ስጦታዎች መበርከታቸውን ከዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.