Fana: At a Speed of Life!

ቱኒዚያ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኟን አሰናበተች

አዲስ አበባ፣ጥር 24፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ቱኒዚያ ከአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ከተሰናበተች በኋላ የብሔራዊ ቡድኑን አሠልጣኝ ሞንደሄር ኬቤየርን አሰናብታለች፡፡

አሠልጣኙ በኳታር የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ሁለት ወራት ሲቀራቸዉ ነዉ ከብሔራዊ ቡድኑ የተባረሩት፡፡

ከነኀሴ 2019 ጀምሮ የቱኒዚያን ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝነት ሲመሩ የቆዩት የ51 ዓመቱ ሞንደሄር ኬቤየር መሰናበታቸዉን ተከትሎ የእርሳቸዉ ምክትል የነበሩት ጃሌል ካድሪ በዋና አሠልጣኝነት ቡድኑን እንደሚመሩት የቱኒዚያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታዉቋል።

ቀደም ሲል የጋና እግር ኳስ ማኅበር ባሳለፍነው ሣምንት አሠልጣኙን ሚሎቫን ራጄቫችን ከብሔራዊ ቡድኑ አሠልጣኝነት ማሰናበቱ የሚታወስ ነዉ።

በፈረንጆቹ 2004 የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን የሆነችው ቱኒዚያ ባደረገችው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች በሁለቱ ብተሸነፍም የሩብ ፍፃሜ ድልድል ውስጥ መግባቷን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.