Fana: At a Speed of Life!

ጠቃሚ የህይወት መርሆወች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የስነ ልቦና ባለሙያዎች አንድ አይነት የህይዎት መርህ ከመከተል ይልቅ በነገሮች ላይ ለቀቅ ማለትና የተለያየ አይነት የህይዎት ዘይቤን መከተል እንደሚገባ ይመክራሉ።

ዕድሜ በራሱ ይዞት ከሚመጣው ለውጥ ባሻገር ባህል፣ አካባቢያዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች በሰው ልጅ የህይዎት ዑደት ላይ በርካታ ለውጦችን ያመጣሉ።

የስነ ልቦና ባለሙያዎች ደግሞ ህይወትን በአግባቡ ለመምራት ይጠቅማሉ ያሏቸወን ሰባት መርሆወች ይጠቅሳሉ፤

ነገሮችን ቀለል አድርጎ ማየት፦ አንድ ነገር ከመከወንዎ በፊት ቀለል ያሉና ዘና የሚያደርጉ እንዲሁም በቀን ውሎዎ ስኬታማ ለመሆን የሚረዱ ነገሮችን መከወን።

ሁሉንም በጥድፊያ ለመስራት ከመሞከር ቀለል አድርጎ መመልከትና የቻሉትን ስራ መስራት።

ለራስ ጊዜ መስጠት፦ ከስራና ወከባ ከበዛበት ህይዎት ባለፈ ለራስ ጊዜ በመስጠት ነገሮችን ለማመጣጠን መሞከር ለተሻለ ስኬትና ህይዎት ይረዳል።

አሉታዊ ሃሳቦችን ከአዕምሮ ማውጣት፦ በአብዛኛው ከስራ ነጻ በሆኑና ብቻዎን በሚያሳልፉበት ጊዜ አዕምሮ በርካታ ነገሮችን ያሰላስላል።

በዚህ መሃል ምናልባትም አዕምሮ አሉታዊ ሃሳቦችን ደጋግሞ ሊያሰላስል ይችላል።

በዚህ ጊዜ ታዲያ ስሜትን ዘና የሚያደርጉ ነገሮችን መከወን እና ከዚህ ስሜት መውጫ የሚሏቸውን መንገዶች መጠቀም መልካም መሆኑንም ይመክራሉ።

በየዕለቱ ትንሽ ለውጥ ለማምጣት ይጣሩ፥ ረጅም መንገድ በአንድ እርምጃ እንደሚጀመር ሁሉ በህይዎትዎ ያሰቡትን ለውጥ ለማሳካት ከቀላሉ ነገር መነሳት ይኖርብዎታል።

ምናልባት ቤት ውስጥ ቀላል ስራዎችን ከውነው የማያውቁ ከሆነ ዛሬውኑ ይጀምሩትና በየዕለቱ ከፍ ወዳለው ስራ ይግቡ።

የጅምር ስራዎች ውጤት ለትልቅ ስኬት መዳረሻም ነውና ድክመቴ ነው ባሉት አንድ ነገርዎ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ዛሬውኑ አንድ ብለው ይጀምሩ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፦ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ለሰውነት እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ብዙ ጊዜ ቢሮ ውስጥ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ከሆነ በሻይ ሰዓት ወጣ ብለው የእግር ጉዞ አድርጎ መመለስ አልያም ባሉበት ቦታ ሆነው ሰውነትን ማዝናናት እጅግ ጠቃሚ ነው።

ይህ አዕምሯዊና ስነ ልቦናዊ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ዘወትር ይከውኑት።

ጤናማ እና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን መመገብ ጤናን ለመጠበቅና የየዕለት ተግባርን በተገቢው መንገድ እና በስኬት ለማጠናቀቅ ይረዳል።

ራስን በስራ መጥመድ፦ ብዙ ጊዜ በስራ የሚጠመዱ ሰዎች የበዛ ትርፍ ሰዓት ካላቸው ሰዎች ጋር ሲነጻጸሩ አይጨናነቁም ለጭንቀትም አይጋለጡም።

ይህ ደግሞ አዕምሮ አንድ ነገር ላይ አተኩሮ በመስራቱ ምክንያት የሚፈጠር አወንታዊ የስራ ጫና ባህሪ መሆኑን ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ራስን በስራ መጥመድ ካልተቻለ ደግሞ መጽሃፍ እያነበቡ አዕምሮን መገንባት አልያም ዘና ያለ ስሜት የሚሰጡዎትን ልማዶች መከወን አማራጭ መሆኑን ይመክራሉ።

እነዚህ የህይዎት መርሆዎች የተሻለ ህይዎት እንዲኖሩ የሚያግዙና በቀላሉ ሊተገብሯቸው የሚችሏቸው አማራጮች ናቸው።

ምንጭ፦ psychologytoday.com

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.